መብራት ኃይል መ/ቤት፣ ኮረንቲ አቋርጦ ውሸት ማከፋፈል ጀምሯል አባይ ሚድያ ዜና፣ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል መ/ቤት ሰሞኑን እጅግ የከበደ ችግር ውስጥ ገብቷል። በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ከሀያ በላይ ትላቅና ትናንሽ ከተሞች ሀይል ተቀርጦባቸዋል። ከናዝሬት /አዳማ/ ከተማ ጀምሮ እስከ ጅጅጋ ድረስ ችግሩ ተንሰራፍቷል። ከነዚህ ከተማዎች ሌላ ሐረርና ድሬዳዋም ኮረንቲው ጸጥ ካለባቸው ትላልቅ ከተሞች መካከል ይጠቀሳሉ። የመብራት ሀይል መ/ቤቱ ለችግሩ መንስኤ ስርቆት ነው በማለት ማስተባበያ እየሰጠ ነው። “አምስት ያክል የኤሌክትሪክ ገመድ ተሸካሚ የሆኑ የብረት ማማዎች በወለንጭቲ አካባቢ ተሰርቆብኛል” በማለት ችግሩን እያስረዳ ነው። ተሰርቀዋል የተባሉት የብረት ማማዎች ሙሉ በሙሉ ይሁን በከፊል እንደተሰረቀ የተብራራ ነገር የለም። ስርቆቱ ከዚህ በፊት በዛው ቦታ ላይ ተፈጽሞ እንደነበር ግን ተናግረዋል። “ተጠርጣሪዎቹ ሌቦች አንድ የብረት ማማ ከላይ እስከታች ቆርጠው እስኪወስዱ ድረስ የአካከቢው ገበሬዎች የት ነበሩ?” ለሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ግን መ/ቤቱ ምንም ምላሽ አልሰጠም። እንደ መ/ቤቱ አገላለጽ ከሆነ ችግሩን አስተካክለው ኮረንቲ ከመቀጠል ይልቅ ሌቦቹን ፈልጎ ማግኘት ላይ ያተኮሩ ይመስላሉ። ይህን ጉዳት ለመተካት መንግስት ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ሊያስወጣው እንደሚችል ቃል አቀባዮቹ ገምተዋል። በነሱ መግለጫ መሰረት ከሃያ በላይ ከተሞች ውስጥ የሚገኝ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ከኤሌክትሪክ ጋር ይቆራረጣል። ምንም እንኳ መ/ቤቱ ችግሩ የተፈጠረው ስርቆት ተፈጽሞብኝ ነው በማለት ለማስተባበል ቢሞክርም አንዳንድ ነጻ ምንጮች ግን ትክክለኛ ችግሩ ያለው ከዋናዎቹ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች ውስጥ ነው ይላሉ። “መ/ቤቱ ሁሌም ክረምቱ አልቆ አዲስ ዓመት በገባ ሰሞን ደጋግሞ የአቅርቦት ችግር ውስጥ እንደሚገባ ይታወቃል” ያሉት ውስጥ አዋቂዎች የወቅቱ ችግር ተመሳሳይ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ይሁንና ያሁኑ ችግር ከበፊቶቹ ሁሉ የከፋ እንደሚሆን ይገምታሉ። ያንን የተገነዘበው መ/ቤቱ ችግሩን በምናቡ በፈጠራቸው ሌቦች ላይ ማሳበብን ከተጠያቂነት እና ከሕዝብ ቁጣ ለማምለጥ ብቸኛ መንገድ ሆኖ አግኝቶታል። አስተያት ሰጪዎች ደግሞ እንዲህ ብለው ይጠይቃሉ፤ ለመሆኑ ሌቦቹ ማንም ሳይደርስባቸው በመጋዝ ገዝግዘው የተባሉትን አምስት ማማዎችን ለመስረቅ ቢችሉ እንኳ ወደሌላ ቦታ ሲያጓጉዙት የጥበቃ ኀይሎች የት ነበሩ? … የተሰረቁትን ለመተካት ብቻ ከሆነ ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ወጪ ለምን አስፈላጊ ሆነ? … እነዚህን ጥያቄዎች በትክክል መመለስ ካልቻለ መ/ቤቱ ኮረንቲ ሳይሆን ውሸት እያከፋፈለ ነው፤ በማለት ሽሙጣቸውን ሰንዝረዋል። ይህ በእንዲህ እያለ በመንግስት ራዲዮኖች በተሰማ ዜና፣ በአዲስ አበባ ከተማ የመብራት ፈረቃ ሊጀመር ነው። የመጀመሪያ ተረኛ የሆኑ አካባቢዎችም በዝርዝር ተገልጠዋል። ማስታወቂያውን የሰሙ የመዲናይቱ ነዋሪዎች “አራቱ ወቅቶች አልፈው አምስተኛው የጨለማ ጊዜ መጣብን” ሲሉ መማረራቸው ተሰምቷል። Recommend on Facebook Tweet about it Subscribe to the comments on this post Print for later Bookmark in Browser Tell a friend ‹ Previous Next › Related posts How Ethiopia Lost Control of Its Teff Genetic Resources Ethiopia: Diaspora Remittance Reach 1.5 billion Dollars a Year መፍትሄ የናፈቃቸው የኑሮ ችግሮች Is Ethiopia ready for foreign investment? (BBC) Leave a Comment Click here to cancel reply. Name* Email* Website Submit Comment