በአንዋር መስጊድ ለጸሎት ከተሰባሰበው አማኝ ይልቅ ፖሊሶች እየበዙ ነው። አባይ ሚድያ ዜና መርካቶ የሚገኘው ታላቁ አንዋር መስጊድ በፖሊስ ኀይሎች ዙሪያውን መከበቡ በርትቷል። ምንም እንኳ የሙስሊሙ ኀብረተሰብ በመንግስት ላይ ያለውን ተቃውሞ በይፋ መግለጽ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አንዋር በታጣቂዎች ጥብቅ ቁጥጥር ሲደረግበት ቢቆይም የዛሬው ግን ለየት ይል ነበር። የዛሬውን የጁምአ ስግደት በተለየ መልኩ በዛ ያሉ የፌዴራል ፖሊሶች አጥለቅልቀውታል። ከፍተኛ ቁጥር ያላው የእስልምና አማኝ እንደወትሮው በአንዋር ግቢ ውስጥ እና ውጭ ጸሎት የማድረግ ባህሉን ከተከለከለ ወራት አልፈዋል። በአሁኑ ወቅት የመስጊዱ አካባቢ የሽብር ቦታዎች ተብለው በመንግስት እጅግ ከሚጠረጠሩ ሥፍራዎች አንዱ ሆኗል። በዚህም ምክንያት ጸሎትና ስግደት በመስጊዱ ግቢ ውስጥ ብቻ እንዲከናወን መንግስት ግዴታ ጥሏል። ይሁንና ለተደጋጋሚ ሳምንታት አማኙ ሁሉ ቢጫ ጨርቅ ክንዱ ላይ በማሰር መንግስት በዓይማኖቱ የግል ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባቱን በፍጥነት እንዲያቆም ቢያስጠነቅቁም ምላሽ አላገኙም። የማስጠንቀቂያው ቢጫ ጨርቅ ወደ ቀዩ የቁጣ ቀለም ይለወጣል ብሎ የሰጋው መንግስት ዛሬ መስጊዱን በከፍተኛ የታጣቂ ሀይል ሲያስጠብቅ እንደነበረ በግልጽ ታይቷል። ሰላማዊው ሙስሊም ኅብረተሰብ ግን በትዕግስት የተሞላውን ማስጠንቀቂያ በአንድነት ካሳየ በኋላ ጸሎቱን አጠናቆ ተበታትኗል። እነሱ ከተበታተኑ በኋላም ግን ፖሊሶች የመስጊዱን ዙሪያ ቶሎ ለቀው ከመሄድ ይልቅ አካባቢውን በዓይነቁራኛና በፍርሃት ሲፈትሹት ቆይተዋል። Recommend on Facebook Tweet about it Subscribe to the comments on this post Print for later Bookmark in Browser Tell a friend ‹ Previous Next › Related posts አዲሱ መጅሊስ ሲጋለጥ ያንብቡት!!! Ethiopian Muslim activists deny terror charges In Defense of Religious Freedom in Ethiopia (Alemayehu G. Mariam) Briefing: Ethiopia’s Muslim protests Leave a Comment Click here to cancel reply. Name* Email* Website Submit Comment